የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያዩ

By Hailemaryam Tegegn

February 14, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ ከ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን ከዋና ጸሐፊው ጋር ዛሬ ማለዳ ተገናኝተናል ብለዋል።

በውይይታቸውም ቅድሚያ በሚሰጣቸው የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ገንቢ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡