አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ቻፖ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ ከ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን ከፕሬዚዳንቱ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል ብለዋል፡፡
ውይይታቸው በከተሞች ልማትና ግብርና፣ ሰላም እና ደህንነትን ጨምሮ በቅድመ ተኮር ዘርፎች መካከል የተጠናከረ የትብብር እድሎችን ለመለየት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።