የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከጄፍሪ ሳክስ (ፕ/ር) ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

February 14, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጄፍሪ ሳክስ (ፕ/ር) ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ ከጄፍሪ ሳክስ (ፕ/ር) ጋር መወያየት ሁልጊዜም አስደሳች ነው ብለዋል፡፡

በውይይታቸውም በዘላቂ ልማት፣ በኢኮኖሚ እድገት እና ለአፍሪካ ልማት የቅድሚያ ጉዳዮችን በተመለከተ መምከራቸውን ተናግረዋል፡፡

ውይይቱ ባለፈው ዓመት ከነበራቸው ውይይት የቀጠለ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አመልክተዋል፡፡