ስፓርት

ማንቼስተር ሲቲ ሳልፎርድ ሰቲን በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ተቀላቀለ

By sosina alemayehu

February 14, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ዋንጫ 4ኛ ዙር በተደረገ ጨዋታ ማንቼስተር ሰቲ ሳልፎርድ ሲቲን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

የማንቼስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ዶሪንግተን (በራስ ላይ) እና ማርክ ጌሂ አስቆጥረዋል፡፡

በሌሎች ጨዋታዎች ዌስትሀም ዩናይትድ ቡርቶን አልቢዮንን 1 ለ 0 ፣ ኖርዊች ሲቲ ዌስትብሮሚች አልቢዮንን 3 ለ 1 እና ማንስፊልድ ታውን በርንሌይን 2 ለ 1 በማሸነፍ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅለዋል፡፡