የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By Adimasu Aragawu

February 15, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ሁለተኛ ቀኑ ላይ በተለያዩ ወሳኝ አጀንዳዎች ውይይታችን እያካሄድን ነው ብለዋል።

ከዚሁ ጎን ለጎን ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ጋር ተገናኝተን በቀጣናዊ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ነው ያሉት።