አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአዲሱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ አዲሱን የሕብረታችን ሊቀመንበር፤ የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬን አግኝቼ በተረከቡት ኃላፊነት ደስታዬን ገልጬላቸዋለሁ ብለዋል።
የአፍሪካውያን ጠንካራ ትብብር እና ቀጣናዊ ግንኙነቶችን ለማሳደግ በሚያስችሉ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገናል ሲሉም ገልጸዋል።