የሀገር ውስጥ ዜና

የቱርክዬ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን አዲስ አበባ ገቡ

By Adimasu Aragawu

February 17, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱርክዬ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን በኢትዮጵያ የሚኖራቸው ቆይታ በኢትዮጵያ እና በቱርክዬ መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ትብብር ይበልጥ ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከ500 ዓመታት የተሻገረ ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ኢትዮጵያ እና ቱርክዬ በአሁኑ ወቅት ጠንካራ የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር አላቸው፡፡

በኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨስትመንት በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ ሀገራት አንዷ የሆነችው ቱርክዬ፤ በተለይም በጨርቃጨርቅ፣ በአግሮ ፕሮሰሲንግና በግብርና ግብዓት ዘርፎች እንዲሁም በዲጂታል መሰረተ ልማት ከፍተኛ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡

ኢትዮጵያ እና ቱርክዬ የሕዝብ ለሕዝብ፣ የታሪክ እንዲሁም የባሕል ትስስር ያላቸው ሀገራት ናቸው።