የሀገር ውስጥ ዜና

ለፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ይፋዊ አቀባበል ተደረገላቸው

By Adimasu Aragawu

February 17, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቱርክዬ ሪፐበሊክ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ይፋዊ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

መሪዎቹ የወል ጥቅም ላይ በተመሰረቱ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።