አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱርክዬ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን የኢትዮጵያ ጉብኝት እያደገ የመጣውን የሁለቱ ሀገራት ስትራቴጂያዊ አጋርነት የሚያጎላ ነው አለ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፡፡
ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለፕሬዚዳንቱ አቀባበል አድርገዋል።
ይህ ጉብኝት በኢትዮጵያ እና ቱርክዬ መካከል እያደገ የመጣውን ስትራቴጂያዊ አጋርነት የሚያጎላ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ማዕከልነት ሚና የሚያረጋግጥ ጉብኝት ነው ብሏል።