አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ የተቀናጀ የምግብ ኢንዱስትሪ ግንባታ አስጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ ዛሬ ያስጀመርነው የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ የተቀናጀ የምግብ ኢንዱስትሪ ግንባታ የበቆሎ እና አኩሪ አተር ዱቄት እንዲሁም 14 ተጓዳኝ የበቆሎ ውጤት ምርቶችን ለማምረት የታቀደ ነው ብለዋል።
ፕሮጀክቱ ተጠናቅቆ ወደ ስራ ሲገባ በቀን 2 ሺህ ቶን በቆሎ እና 120 ቶን አኩሪ አተር የማምረት አቅም እንደሚኖረው ገልጸዋል።
ከ6 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ሠራተኞች ቋሚ እና ጊዜያዊ የሥራ እድል እንደሚፈጥርም አመልክተዋል።
ፕሮጀክቱ ለአካባቢው አርሶአደሮች፣ ለኅብረት ሥራ ማኅበራት እና የግል ዘርፍ አምራቾች የእሴት ሰንሰለትን በማገዝ ሰፊ ገበያ ይፈጥራል፤ የአካባቢውን ኢኮኖሚ ያሳድጋል ሲሉም አስረድተዋል።