የሀገር ውስጥ ዜና

የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ተጠናቀቀ

By Hailemaryam Tegegn

February 21, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለተከታታይ ሦስት ቀናት በልዩ ልዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሲካሄድ የቆየው የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ተጠናቋል።

በሀገራዊና የፓርቲ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት ያካሄደው የፓርቲው ምክር ቤት ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን ማስቀመጡን አስታውቋል፡፡