የሀገር ውስጥ ዜና

‎የኮሪደር ልማት ስራዎች እያደገ ለመጣው ከተሜነት ሀገርን ያዘጋጁ ሆነዋል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

By Hailemaryam Tegegn

February 21, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‎‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኮሪደር ልማት ስራዎች እያደገ ለመጣው ከተሜነት ሀገርን ያዘጋጁ ሆነዋል አሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ በሐዋሳ ከተማ በሁለተኛው ምዕራፍ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎችን በዛሬው ዕለት ተመልክተናል ብለዋል።

የኮሪደር ልማት ስራዎች የተሻለ ሀገርን ለትውልድ የመገንባት አካል ሆነው በርካታ ከተሞችን እየለወጡ ይገኛሉ ነው ያሉት።

አጠቃላይ ስራዎቹ እያደገ ለመጣው ከተሜነት ሀገርን ያዘጋጁ መሆናቸውንም አመልክተዋል።