አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት የጨዋታ መርሐ ግብር አርባምንጭ ከተማ እና ነጌሌ አርሲ አቻ ተለያይተዋል።
ቀን 9 ሰዓት ላይ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የተካሄደው የአርባምንጭ ከተማ እና ነጌሌ አርሲ ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል።
በጨዋታው የነጌሌ አርሲን ግብ በመጀመሪያው አጋማሽ ዳዊት ተፈራ ሲያስቆጥር በፍቅር ግዛቸው ለአርባምንጭ ከተማ የአቻነቷን ግብ ከመረብ አሳርፏል።
በተመሳሳይ ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው የሐዋሳ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።
የሐዋሳ ከተማን ግብ ሽመልስ በቀለ ሲያስቆጥር የድሬዳዋ ከተማን ግብ ደግሞ ድልአዲስ ገብሬ ከመረብ አሳርፏል።
የሊጉ መርሐ ግብር ቀጥለው ሲደረጉ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ ሸገር ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ይገናኛል።
እንዲሁም በተመሳሳይ ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።