የሀገር ውስጥ ዜና

የእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ አዲስ አበባ ገቡ

By Adimasu Aragawu

February 25, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንቱ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ ከመንግሥት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።