ቢዝነስ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለሀገራዊ ልማት…

By Adimasu Aragawu

February 25, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች በኢትዮጵያ የስራ እድል በመፍጠር እና ሀገራዊ ልማትን በማገዝ ረገድ የሚበረክተው አስተዋጽዖ እያደገ መጥቷል አለ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን።

ኮርፖሬሽኑ በመንግሥት እና በግል ባለሀብቶች የለሙ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለሀገር ልማት ያደረጉትን አስተዋጽዖና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በተመለከተ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በመላው ሀገሪቱ በሚያስተዳድራቸው 14 ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከ290 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ባለሃብቶች መሰማራታቸው በመድረኩ ተገልጿል።

በዚህም የውጭ ምንዛሪ ግኝትን በማሳደግ፤ ለወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማምጣት፣ ተኪ ምርቶችን በማምረት እና በየአካባቢው ለሚገኙ አርብቶ እና አርሶ አደሮች ዘላቂ የሆነ የገበያ ትስስር መፍጠር መቻላቸው ተመላክቷል፡፡

በይስማው አደራው