አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ለይፋዊ ጉብኝት የመጡትን የእስራኤል ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግን ተቀብዬ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
በውይይቱም የኢትዮጵያና እስራኤልን ግንኙነት በማጤን በወል ፍላጎታችን ላይ ተመስርተን ትብብራችንን የምናሳድግባቸውን መንገዶች ተመልክተናል ነው ያሉት፡፡