አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ሳንኩራ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል።
የሳንኩራ ወረዳ ፖሊስ ትራፊክ ዋና ስራ ሒደት አስተባባሪ ሳጂን አብዱልሽኩር ሀምዳላ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ የትራፊክ አደጋው በወረዳው ረግዲና ማዞሪያ ከተማ ወደ ሀላባ የሚሄድና ከሀላባ የሚመለስ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ በተለምዶ ዶልፊን ተብሎ ከሚጠራው ሚኒባስ ጋር በመጋጨቱ የደረሰ ነው።
አደጋው በዛሬው ዕለት ከረፋዱ 5 ሰዓት ከ20 ደቂቃ አካባቢ መከሰቱን ገልጸው÷ በአደጋው የ5 ሰዎች ሞት፣ 2 ከባድና 2 ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።
በትራፊክ አደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በአቅራቢያው በሚገኙ የጤና ተቋማት ህክምና እየተከታተሉ መሆናቸውን አስረድተዋል።
የትራፊክ አደጋው መንስዔ በፍጥነት ማሽከርከር መሆኑን ጠቅሰው ተጨማሪ የማጣራት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በአድማሱ አራጋው