ስፓርት

አርባምንጭ ከተማ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

By Mikias Ayele

February 27, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ21ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አርባምንጭ ከተማ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡

አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ አርባምንጭ ከተማ ባህርዳር ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ቡጣቃ ሸመና እና ይድነቃቸው ያሲን የአርባምንጭን የማሸነፊያ ግቦች አስቆጥረዋል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፋሲል ከነማን 2 ለ 1 በማሸነፍ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።

የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኤፍሬም ሃ/ማርያም እና ኮንኮኒ ሀፊዝ ሲያስቆጥሩ፤ ፋሲል ከነማን ከሽንፈት ያልታደገውን ብቸኛ ግብ ጃቢር ሙሉ ከመረብ አሳርፏል።