አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 28ኛ ሳምንት የጨዋታ መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ ከመሪው አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል።
በሊጉ ዛሬ 5 ጨዋታዎች ሲደረጉ ምሽት 2፡30 ሰዓት ላይ ማንቼስተር ሲቲ ከሜዳው ውጪ በመጓዝ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ይጫወታል።
ከአርሰናል በአምስት ነጥብ ተበልጠው ሁለተኛ ደረጃ የሚገኙት ውሃ ሰማያዊዎቹ የነጥብ ልዩነቱን ለማጥበብ ነው ወደ ሜዳ የሚገቡት።
ከዚህ ጨዋታ ቀደም ብሎ አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 6ኛ ላይ የሚገኘው ሊቨርፑል ከወራጅ ቀጣና ለመውጣት እየታገለ ከሚገኘው ዌስትሃም ጋር ይገናኛል።
በተመሳሳይ ሰዓት ኒውካስል ከኤቨርተን እንዲሁም በርንሌይ ከብሬንትፎርድ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
እንዲሁም ቀን 9:30 ላይ በሁለት ነጥብ ልዩነት በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ 8ኛ እና 12ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት በርንማውዝ እና ሰንደርላንድ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ትናንት በተደረገው የ28ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታ ወልቭስ አስቶንቪላን 2 ለ 0 አሸንፏል።