ስፓርት

አትሌት ታደሰ ታከለ የ2026 የቶኪዮ ማራቶንን አሸነፈ

By Hailemaryam Tegegn

March 01, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዛሬ በተካሄደው የ2026 የቶኪዮ ማራቶን የባለፈው ዓመት የውድድሩ አሸናፊ ታደሰ ታከለ በበላይነት አጠናቋል፡፡

አትሌት ታደሰ በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ በተሰጠው የቶኪዮ ማራቶን ለተከታታይ ሁለተኛ ጊዜ አሸናፊ መሆን ችሏል፡፡

ኬንያውያኑ ኪፕቹምባ እና ሙንያዎ 2ኛ እና 3ኛ በመሆን ሲያጠናቅቁ፥ ኢትዮጵያውያኑ ሙክታር ኢድሪስ 5ኛ፣ሰለሞን ባረጋ 7ኛ እንዲሁም ሴፉ ቱራ 8ኛ እና ሽፈራው ታምሩ 10ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

በሴቶች ኬንያዊቷ ብሪጂድ ኮስጌ 1ኛ በመሆን ስታጠናቅቅ፥ ኢትዮጵያውያኑ ብርቱካን ወልዴ፣ ሀዊ ፈይሳ፣ ሱቱሜ አሰፋ እና መገርቱ አለሙ ከ2 እስከ 5 ያለውን ደረጃ በመያዝ ተከታትለው ገብተዋል፡፡