የሀገር ውስጥ ዜና

130ኛው የዓድዋ ድል በዓል እየተከበረ ነው

By sosina alemayehu

March 02, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 130ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ከአኩሪ ታሪክ ወደ ብሩህ አድማስ” በሚል መሪ ሐሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተከበረ ይገኛል።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በዓሉን አስመልክቶ በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ሐውልት እና በዓድዋ ጀግኖች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

በበዓሉ አከባበር ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ (ኢ/ር) እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተገኝተዋል።

እንዲሁም የጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ፣ ሚኒስትሮች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮችን ጨምሮ የመከላከያ ሠራዊት አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በመርሐ ግብሩ የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንቶች ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) እና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪይም ደሳለኝ ታድመዋል።

በግዛቸው ግርማዬ