የሀገር ውስጥ ዜና

የአየር ንብረት ለውጥ በቀጣናው ሀገራት ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለመመከት…

By sosina alemayehu

March 02, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ‎ዓለም አቀፉ የአካባቢ ጥበቃ ተቋም ‎የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ዐውደ ጥናት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

ዐውደ ጥናቱ የአየር ንብረት ለውጥ በቀጣናው ሀገራት ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለመመከት የሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ለተከታታይ ሦስት ቀናት እንደሚቆይ ተመላክቷል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መኮንን በመድረኩ ላይ እንዳሉት÷ አፍሪካውያን የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮች ገፈት ቀማሽ ከመሆን ተሻግረን መፍትሔ አመንጪ ልንሆን ይገባል።

በዚህም ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ ችግሮች መፍትሔ የሚሆኑ ስራዎችን በማከናወን አመርቂ ውጤት እያስመዘገበች ትገኛለች ብለዋል።

ለዚህም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር፣ የታዳሽ ኃይልን ለማመንጨት የሚያስችለውን ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማጠናቀቋ፣ ከተሞችን አረንጓዴያማ ማድረጓ፣ የወንዝ ዳር ልማት እና መሰል ስራዎችን ለአብነት አንስተዋል።

የዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ፈንድ የአፍሪካ አስተባባሪ ጆንኪ ቴኑ በበኩላቸው÷ የቀጣናው ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ ምንም ሚና ባይኖራቸውም የችግሩ ገፈት ቀማሽ መሆናቸውን አስረድተዋል።

የአፍሪካ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ በሚያመጣቸው ድርቅ፣ ረሃብ እና ሌሎች ችግሮች ተጋላጭ መሆናቸውን ጠቅሰው÷ ችግሩን መከላከል የሚቻልበት ሁኔታዎች በመፈጠር ላይ እንደሆኑ ተናግረዋል።

በቅድስት አባተ