አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዓለም ሚሊተሪ ሀገር አቋራጭ ውድድር የመቻል አትሌቲክስ ቡድን የወርቅ ሜዳልያ አሸንፏል፡፡
የመቻል አትሌቲክስ ቡድን የወርቅ ሜዳልያውን ያሸነፈው በግሪክ ትሪካላ ከተማ 38 ሀገራት በተሳተፉበት 60ኛው የዓለም ሚሊተሪ ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ውድድር ላይ ነው።
ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፉት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መቻል ስፖርት ክለብ አትሌቶች በድብልቅ ሪሌ አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳልያ አግኝተዋል፡፡
ተወዳዳሪዎቹ አምሳ አለቃ ደጀኔ ተሾመ፣ አስር አለቃ ዮብሰን ብሩ መሠረታዊ ወታደር መሠረት ሙሉጌታ እና መሠረታዊ ወታደር ጫልቱ ታደሰ ናቸው።