ስፓርት

የስፖርት ዲፕሎማሲና የስፖርት መሰረተ ልማት ስራችን ፍሬ እያፈራ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

By abel neway

March 04, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና የስፖርት ዲፕሎማሲ እንዲሁም የስፖርት መሰረተ ልማት ስራችን ፍሬ እያፈራ ነው አሉ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ ውድድር በአዲስ አበባ ለማዘጋጀት ዕድል በማግኘቷ በዓለም አትሌቲክስ ካላንደር ውስጥ መካተት መቻሏን ጠቅሰዋል።

ውድድሩ በፈረንጆቹ ሚያዚያ 18 ቀን 2026 የሚከናወን መሆኑን ገልጸው፤ ውድድሩ ለሀገራችን ብሎም ለአትሌቲክስ ባለሙያዎች ትልቅ እድል ነው ብለዋል።

ይህ ትልቅ ውጤት እንዲመዘገብ የለፋችሁ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ ገልጸዋል።

የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ሀገሪቱ ዓለም አቀፍ ውደድሮችን ለማዘጋጀት በቂ አቅም እንዳላት ገልጸው፤ የተለያዩ ውድድሮችን ወደ ኢትዮጵያ እናመጣለን ማለታቸው ይታወሳል።