ቴክ

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በትብብር ለመስራት ተስማሙ

By Yonas Getnet

March 06, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።

ተቋማቱ ባደረጉት ትብብር መሰረት አንድ ሚሊየን ብር ሽልማት የሚያስገኝ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሙዚቃ ውድድር ያካሂዳሉ።

በዚህም የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና እሁድ ኤ.አይ ስቱዲዮ በጋራ በመሆን የኤ.አይ የሙዚቃ ውድድር አዘጋጅተዋል፡፡

የውድድሩ ዓላማ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የኢትዮጵያን የጀግንነት ታሪክ በተለይም የዓድዋ ድልን ለመዘከር እንደሆነ ተገልጿል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያን የፈጠራ ኢንዱስትሪ ወደ አዲስ የቴክኖሎጂ ምዕራፍ ለማሸጋገር ያለመ እንደሆነ ተመላክቷል።

በውድድሩ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ስራዎቻቸውን እስከ መጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እዲያስረክቡ ጥሪ ቀርቧል።

👉 ለበለጠ መረጃ እና ስራዎችን ለማስረከብ፡- https://www.creativeaward.ai/ ይጎብኙ!