የሀገር ውስጥ ዜና

“የምርጫዬ” መተግበሪያ አጠቃቀም …

By Mikias Ayele

March 06, 2026

 

  1. “ምርጫዬ” የተሰኘውን የመራጮች መመዝገቢያ መተግበሪያ ከPlay Store / APP Store በማውረድ በስልክዎ ላይ ይጫኑ፣

 

  1. በስልክዎ ላይ ከተጫኑ ዝርዝር መተግበሪያዎች ውስጥ “ምርጫዬ” የሚለውን መተግበሪያ ይክፈቱ፣

 

  1. በመቀጠልም ከተከፈተው የ“ምርጫዬ” መተግበሪያ ላይ የሚጠቀሙበትን ቋንቋ ይምረጡ፣

 

  1. ቋንቋ መርጠው ከገቡ በኋላ ከሚያገኟቸው ዝርዝሮች ውስጥ “የእርስዎን መገለጫ ይፍጠሩ” የሚለውን ይጫኑ፣

 

 

  1. በመቀጠል “በፋይዳ አማካኝነት ወደ መለያ” የሚለውን አማራጭ ይጫኑ፣

 

  1. የፋይዳ ገጹ ሲመጣልዎ ከፋይዳ መታወቂያዎት ላይ 16 አኅዝ ያለውን ቁጥር (FAN) ካስገቡ በኋላ በስልክዎ የሚላክልዎን ባለስድስት አኅዝ የአንድ ጊዜ ማረጋገጫ ቁጥር (OTP) ይሙሉ፣

 

  1. መረጃዎን ከፋይዳ ሲያገኙ “ይቀጥሉ” የሚለውን በመጫን መተግበሪያው የሚጠይቅዎትን ቀሪ መረጃ በማስገባት መስማማትዎን በሳጥኑ ውስጥ ምልክት ያድርጉ፣

 

  1. በመቀጠል ያስገቡትን መረጃ ወደ መተግበሪያው ለመላክ “አስገባ” የሚለውን በመጫን ከመተግበሪያው ቋሚ የመራጭነት መለያ ቁጥር ያገኛሉ፤ ይህ ሊይዙት የሚገባ ቋሚ የመራጭነት መለያ ቁጥርዎ ነው፣

 

  1. ያስታውሱ! ቋሚ የመራጭነት መለያ ቁጥር አገኙ ማለት ምዝገባዎ ተጠናቋል ማለት አይደለም “ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ይመዝገቡ” የሚለውን መጫን ይኖርብዎታል፣

 

  1. በመቀጠልም በአድራሻዎ መሠረት ቅርብ የሆነ የምርጫ ጣቢያ ለመምረጥ የምርጫ ጣቢያ ዝርዝር ያገኛሉ፣

 

  1. ከሚያገኙት የምርጫ ጣቢያ ዝርዝሮች ውስጥ የሚቀርብዎን የምርጫ ጣቢያ በመምረጥ “ይመዝገቡ” የሚለውን ይጫናሉ፣

 

  1. በመረጡት ምርጫ ክልል በኗሪነት ያልዎትን ቆይታ በዓመት እና በወር ያስገባሉ። ያስገቡትን መረጃ ትክክለኛነት በማረጋገጥ በሳጥኑ ላይ ምልክት በማድረግ ያረጋግጡ የሚለውን በመጫን ለምርጫው እራስዎን ይመዘግባሉ፣

 

  1. በመቀጠል የመታወቂያዎን ዓይነት በመምረጥ የመረጡትን መታወቂያ ፊት እና ጀርባ ፎቶ ማንሣት እና ማያያዝ፣

 

  1. መቀጠል ለምርጫ ቀን ይዘው የሚመጡት ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል የምርጫ ካርድ ከ48 ሰዓት በኋላ ከመተግበሪያው ያገኛሉ፣

 

 

  1. ምርጫ ካርድዎን አትመው ለመያዝ “ወደ ዋና ገጽ ይመለሱ” የሚለውን አማራጭ በመጫን ዋና ገጽ ላይ የሚገኘውን “ያትሙ” የሚለውን አማራጭ መጫን ይኖርብዎታል።