የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ኢዮብ መሳፍንት የኢዜማ መሪ ሆነው ተመረጡ

By Hailemaryam Tegegn

March 08, 2026

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አቶ ኢዮብ መሳፍንት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) መሪ የነበሩትን ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በመተካት የፓርቲው መሪ ሆነው ተመረጡ፡፡

ፓርቲው በዛሬው ዕለት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማኒፌስቶውን ያስተዋወቀ ሲሆን፥ በቀጣይ የሚመራበትን 50 ፖሊሲዎችንም ለአባላቱ ይፋ አድርጓል፡፡

ፖሊሲዎቹ በተለይም በሀገር መንግስት ግንባታ፣ በብሔራዊ ጥቅም፣ ልማትና ኢኮኖሚ እንዲሁም በአካታችነትና ሌሎች ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ኢዜማ በአስቸኳይ ስብሰባው እዮብ መሳፍንትን የፓርቲው መሪ እንዲሁም ንጋቱ ወልዴን ምክትል መሪ በማድረግ የመረጠ ሲሆን፥ የቀድሞውን የፓርቲው መሪ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እና ምክትላቸውን በክብር ሸኝቷል።

በታምራት ደለሊ