የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሁለት ባለ 9 ወለል ሕንጻዎችን ግንባታ አስጀመሩ

By Melaku Gedif

March 11, 2026

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሁለት ተጨማሪ ባለ 9 ወለል ሕንጻዎችን ግንባታ አስጀምረዋል፡፡

ከንቲባዋ ÷ ዛሬ ደሳሳ ቤቶችን በማንሳት የሁለት ተጨማሪ ባለ 9 ወለል ሕንጻዎች ግንባታ ለማስጀመር የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥራ አከናውነናል ብለዋል።

አምስት ነባር ቤቶችን በማንሳት በምትካቸው የተገነባው ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንት መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ይህም ቀድመው በቦታው ይኖሩ ለነበሩት ብቻ ሳይሆን በአካባቢው በደሳሳ የቀበሌ ቤቶች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ ለነበሩ ወገኖች ጭምር እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

ቤት የማስተላለፊያ ሥርዓቱ በመሰረታዊ ሪፎርም ሥራና አሰራሩን ግልፅ በማድረግ ዕጣው በሕዝብ ፊት ወጥቶ ለነዋሪዎች ማስረከብ መቻሉን አመልክተዋል፡፡

የግንባታ ወጪውን በመሸፈን በትብብር ለመገንባት ቃል ለገቡት አዋሽ ባንክና ኤም ኤን አር ሲ ጥሬ እቃዎች አስመጪና ላኪ ድርጅት ምስጋና አቅርበዋል