የሀገር ውስጥ ዜና

መገናኛ ብዙሃን የሀገርና የሕዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል – ሙዓዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

By sosina alemayehu

March 12, 2026

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መገናኛ ብዙሃን የሀገርና የሕዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል አሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማሕበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሙዓዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፡፡

መገናኛ ብዙሃን በሀገር ብሔራዊ ጥቅም ላይ ያላቸውን ሚና የሚዳስስ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ሙዓዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በሀገር ግንባታ ሒደት ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ሚና ጉልህ ነው፡፡

የወል ትርክትን በመገንባት የሕዝብ የጋራ እሴቶችን በማጎልበትና ሀገራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃይማኖት ዘለቀ በበኩላቸው፥ መገናኛ ብዙሃን ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በማቅረብ ለሀገር ግንባታ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ገልጸዋል።

በመድረኩ በኢትዮጵያ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን ብሔራዊ ጥቅምን መሠረት ያደረጉ ሥራዎችን በመስራት ረገድ ያሉበትን ደረጃ የሚዳስስ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በቤተልሔም መኳንንት