አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት በደረሰው ጉዳት ሀዘናቸውን ገልጸዋል።
ከንቲባዋ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው የመሬት መንሸራተት እና የጎርፍ አደጋ በወገኖቻችን ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እገልጻለሁ ብለዋል።
በአደጋው ለተጎዱ ቤተሰቦች፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለመላው የክልሉ ህዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል።
በቀጣይም በአደጋው የተጎዱ ወገኖቻችንን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ሁሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ሕዝብ ከጎናችሁ የሚቆም መሆኑን አረጋግጣለሁ ነው ያሉት።