የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከሼኽ ሞሃሙድ ቢን ራሺድ አል መክቱም ጋር ተወያዩ

By sosina alemayehu

March 14, 2026

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዱባይ ገዥ፣ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ምክትል ፕሬዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ሼኽ ሞሃሙድ ቢን ራሺድ አል መክቱም ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ በዛሬው ዕለት ሼኽ ሞሃሙድ ቢን ራሺድ አል መክቱምን አግኝቼ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

‎በሁለቱ ሀገሮቻችንና ሕዝቦቻችን መካከል ስላለው ጠንካራ የቢዝነስ፣ ትምህርትና ባህል ትስስር ተነጋግረናልም ነው ያሉት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህች ጠንካራ፣ ውብ እና ጽኑ ከሆነችው ዱባይ ከተማ ጋር ያለን ትስስር በቀጣይ ጉብኝቶችም ይጠናከራል ሲሉ አመልክተዋል።