የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 3.95 በማምጣት የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚዋ ዶ/ር ሜሮን ለገሰ

By Melaku Gedif

March 14, 2026

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዶክተር ሜሮን ለገሰ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ት/ቤት 3.95 አማካይ ውጤት በማምጣት የከፍተኛ ውጤትና የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ ሆናለች፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት በተለያዩ የሕክምና ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 263 አዳዲስ ባለሙያዎችን አስመርቋል፡፡

ዶ/ር ሜሮን ለገሰ ከሕክምና ት/ቤት 3.95 አማካይ ውጤት በማምጣት የከፍተኛ ውጤት እና የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ መሆን ችላለች፡፡

ዶ/ር ሜሮን በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሴት ተማሪዎች ውጤታማነትና ተሳትፎ እየተሻሻለ መምጣቱን ተናግራለች፡፡

በዘርፉ ያገኘችውን እውቀት ለሀገሯና ለወገኖቿ በቅንነት ለማገልገል ዝግጁ እንደሆነች መግለጿንም የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል፡፡