ስፓርት

ኢትዮጵያ መድን አርባ ምንጭ ከተማን አሸነፈ

By abel neway

March 14, 2026

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ24ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን አርባ ምንጭ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የኢትዮጵያ መድንን የማሸነፊ ግቦች ወገኔ ገዛኸኝና አማኑኤል ኤርቦ አስቆጥረዋል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ድሬዳዋ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና አዳማ ከተማን 3 ለ 2 አሸንፏል፡፡

የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች ዘላለም አባተ፣ በፍቃዱ አለማየሁ እና ሀምዛ ሱልጣን ሲያስቆጥሩ የአዳማ ከተማን ግቦች ደግሞ አህመድ ሁሴን (2) ከመረብ አሳርፏል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀዋሳ ከተማን 4 ለ 2 ማሸነፍ ችሏል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የማሸነፊያ ግቦች ናትናኤል ዳንኤል፣ አዲስ ግደይ(ፍ)፣ ሁዘፋ ሻይፊ እና ሲሞን ፒተር አስቆጥረዋል፡፡