የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የሀገር ውስጥ ተርሚናል ማስፋፊያ ተመረቀ

By Yonas Getnet

March 15, 2026

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የሀገር ውስጥ ተርሚናል ማስፋፊያ ተመርቋል፡፡

በመርሐ ግብሩ የአየር መንገዱ የቦርድ አባላት፣ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን የተቋሙ መረጃ አመልክቷል፡፡