የሀገር ውስጥ ዜና

ሳዑዲ ዓረቢያ በጋሞ ዞን በደረሰው አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማትን ሐዘን ገለጸች

By Yonas Getnet

March 16, 2026

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሳዑዲ ዓረቢያ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማትን ሐዘን ገልጻለች፡፡

የሳዑዲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ መንግሥት ባስተላለፈው የሐዘን መግለጫ መልዕክት÷ በጋሞ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በተከሰተው አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማውን ሐዘን ገልጿል፡፡

ሚኒስቴሩ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች ቤተሰቦች መጽናናትን በመመኘት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች በፍጥነት እንዲያገግሙ መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡

በጋሞ ዞን የካቲት 30 እና መጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም የጣለው ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍና የመሬት ናዳ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡

በተከሰተው አደጋም እስከ ትናንትናው ዕለት ድረስ የ81 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የጋሞ ዞን መረጃ አመልክቷል፡፡