የሀገር ውስጥ ዜና

ወደ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት እስክንመለስ ድረስ ነዳጅን በቁጠባ መጠቀም ይገባል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

By Yonas Getnet

March 19, 2026

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ወደ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት እስክንመለስ ድረስ ነዳጅን በቁጠባ መጠቀም ይኖርብናል አሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡

ከንቲባዋ እንዳሉት ÷በአሁኑ ወቅት በመካከለኛው ምሥራቅ በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት ሀገራችንን ጨምሮ ነዳጅ ገዝተው የሚጠቀሙ ሀገራት አቅርቦቱን እንደልብ ለማግኘት ተቸግረዋል።

ስለሆነም የከተማዋ ነዋሪዎች ችግሩ ተፈትቶ ወደ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት እስክንመለስ ድረስ ነዳጅን በቁጠባ መጠቀም አለባቸው ነው ያሉት፡፡

የከተማዋ ነዋሪዎች አጫጭር መንገዶችን በእግር በመጓዝ እንዲሁም የብስክሌት አማራጮችን እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም እንዲተባበሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡