አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የ2026 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴት የቢዝነስ መሪ እውቅና አግኝተዋል፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ መቀመጫውን እንግሊዝ ለንደን ባደረገው አፍሪካ ቢዝነስ መጽሔት የ2026 የአፍሪካ ሴት የቢዝነስ መሪዎች ዝርዝር ውስጥ መካተት ችለዋል፡፡
ፍሬሕይወት ታምሩ ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ የቴሌኮምና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ ላስመዘገቡት የላቀ ስኬትና ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እውቅናው እንደተሰጣቸው ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም ኢትዮ ቴሌኮም መደበኛ የቴሌኮም አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር ሁለገብ የዲጂታል ተጠቃሚነትና የኢኮኖሚ እድገትን ለማረጋገጥ የላቀ ሚና እንዲወጣ ማስቻላቸው ነው የተገለጸው፡፡