አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ ወታደሮቿን ወደ መካከለኛው ምስራቅ የመላክ እቅድ እንደሌላት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ፡፡
ኢራን ከአሜሪካ እና እስራኤል ጋር ወደ ግጭት የገባችበት የቀጣናው ውጥረት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን፥ በተለይም የኢነርጂ መሰረተ ልማቶችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች እየተፈጸሙ ይገኛሉ፡፡
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጦርነቱ ተባብሶ መቀጠሉን ተከትሎ አሜሪካ ተጨማሪ እግረኛ ወታደሮችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለመላክ እያጤነች ነው መባሉን ውድቅ አድርገዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በዛሬው ዕለት ከጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሳናይ ታካይቺ ጋር በኋይት ሀውስ ካደረጉት ውይይት በኋላ በሰጡት አስተያየት ወታደሮቻችንን ወደየትም አናሰማራም ብለዋል፡፡
ነገር ግን ሀገራቸው እንደ አስፈላጊነቱ የትኛውንም ርምጃ ልትወስድ እንደምትችል መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡