አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በጊምባ እና መካነሰላም ግቢ በ6ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 698 ተማሪዎች አስመርቋል።
ዩኒቨርሲቲው ካስመረቃቸው ተማሪዎች ውስጥ 241 ሴቶች ናቸው።
ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ሲያስመርቅ 51A+ እና ስድስት A በማምጣት አራት ነጥብ በማስመዝገብ ተማሪ ቃልኪዳን ታዘብ ከተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ክፍል የማዕረግ እንቁ ተሸላሚ ሆናለች።
ተግቶ መሥራት የዛሬ ስኬቴ መሰረት ነው ያለችው ተማሪ ቃልኪዳን በውጤቷ መደሰቷን ገልጻለች፡፡
በዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ የመምህራን እና የወላጆቿ ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደነበረው ተናግራለች፡፡
ተማሪ ቃልኪዳን ከመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ከሁለቱም ግቢ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ አጠቃላይ የሁለት ዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች።
የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ሴኔትም ለዚህ ስኬቷ ተማሪ ቃልኪዳን በዩኒቨርሲቲው በመምህርነት እንድታገለግል እና የትምህርት እድል እንድታገኝ ወስኗል፡፡