ዓለምአቀፋዊ ዜና

በኳታር የወታደራዊ ሄሊኮፕተር ላይ በደረሰ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ

By Yonas Getnet

March 22, 2026

‎አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዛሬው ዕለት በኳታር የወታደራዊ ሄሊኮፕተር ላይ በደረሰ የመከስከስ አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት አልፏል።

የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው÷ ሄሊኮፕተሩ የተከሰከሰው በመደበኛ ሥራ ላይ እያለ በተፈጠረው የቴክኒክ ችግር ነው።

በዚህም በሄሊኮፕተሩ ላይ የነበሩ ሰባት ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ሚኒስቴሩ መግለጹን አልጀዚራ ዘግቧል።

ከሟቾቹ ውስጥ ሦስት የቱርኪዬ ሲቪሎችና አንድ የቱርኪዬ ወታደር እንዳሉበት የኳታር እና የቱርኪዬ መከላከያ ሚኒስቴሮች ባወጡት መረጃ ገልጸዋል።

የአደጋውን ትክክለኛ መንስኤ ለማወቅ ተጨማሪ ምርመራ እንደሚካሂድ መገለጹንም ዘገባው አመልክቷል።

በአድማሱ አራጋው