የሀገር ውስጥ ዜና

የ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ለአካባቢው ማህበረሰብ ሰፊ የስራ ዕድል የፈጠረ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

By Adimasu Aragawu

March 22, 2026

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ለአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ያለው ቅርበ የጎብኝዎችን ምቾት ከመጨመሩም በላይ ለአካባቢው ማህበረሰብ ሰፊ የስራ ዕድልን የፈጠረ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት በፍራፍሬ እና በደን ዛፎች የተከበበውን የ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

የ‘ኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ’ ለአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ያለው ቅርበ የጎብኝዎችን ምቾት ከመጨመሩም በላይ ለአካባቢው ማህበረሰብ ሰፊ የስራ ዕድልን የፈጠረ ነው ሲሉም በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት አመላክተዋል።