የሀገር ውስጥ ዜና

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች በ10 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ

By Adimasu Aragawu

March 25, 2026

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች በ10 ሚሊየን ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በዞኑ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ክልሉ አጋርነቱን ለማሳየት በ10 ሚሊየን ብር የሚገመት ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ እንዲሁም ለቤት መስሪያ የሚሆን የዓይነት ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።

ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው÷ በአደጋ ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አበባዬሁ ታደሰ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ላሳየው ወገናዊነት ምስጋና በማቅረብ አደጋው ከደረሰ ጊዜ ጀምሮ መላው ኢትዮጵያውያን የአቅማቸውን ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።

በዚህም የቆየ የኢትዮጵያውያን መተሳሰብና መደጋገፍ ባህል የታየበት መሆኑን መናገራቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙኒኬሽን ለፋና ዲጂታል ገልጿል።