ስፓርት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔን አሸነፈ

By Mikias Ayele

March 27, 2026

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔን 3 ለ 0 አሸንፏል።

በሞሮኮ ኤል አብዲ ስታዲየም ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ የዋልያዎቹን የማሸነፊያ ግቦች አቤል ያለው (2) እና ከነዓን ማርክነህ አስቆጥረዋል።

መልሱ ጨዋታ በቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ በድሬዳዋ ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል።