አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከማዕከል እስከ ወረዳ ካሉ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
ከንቲባዋ በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕከት÷ ዛሬ ከማዕከል እስከ ወረዳ ካሉት አመራሮቻችን ጋር ሰፊ ውይይት አካሂደን ግልፅነት ፈጥረናል ብለዋል።
በውይይቱ ከሃይማኖት ተቋማት ጋር በተደረጉ ውይይቶች የተነሱ ጥያቄዎችና ቅሬታዎችን ለመመለስ የከተማ አስተዳደሩ ባዘጋጀው የማስፈጸሚያ ዕቅድ ላይ የጋራ መግባባት መደረሱን ገልጸዋል፡፡
ለዕቅዱ ተፈጻሚነትም አስፈላጊውን ስምሪት መስጠታቸውን ገልጸው÷ አፈጻጸሙንም በቅርብ የምንከታተል ይሆናል ነው ያሉት።