የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By Hailemaryam Tegegn

March 30, 2026

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዚዳንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ንጉሜ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ታዬ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ ከአፍሪካ፣ ካሪቢያን እና የፓስፊክ መንግስታት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡

ውይይቱ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነትና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው፡፡