አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት አስመልክቶ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።
በሰልፉ ላይ የሐይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎችን ጨምሮ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
ሰልፈኞቹ በመልዕክቶቻቸው በመጋቢት 24 ተምሳሌታዊ ጉዞ እና መሰረታዊ ርምጃ የተመዘገቡ ስኬቶችን እያደነቁ ነው።
በለውጡ መንግሥት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ተግባራትን በመደገፍ፣ በቀጣይም የተሻለ ስራ እንዲሰራ ከመንግሥት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ የሚያረጋግጡ መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛሉ።
በዚህም በመጋቢት 24 ፍሬ ወደ ተምሳሌታዊ ጉዞ፣ ጠንካራ መሰረት የተምሳሌትነት ጉዞ ስንቅ፣ መሰረት ባለው ርምጃ ወደ ተምሳሌትነት፣ መጋቢት 24 የተምሳሌታዊነታችን መሰረትና መፍለቂያ ነው፣ የመጋቢት 24 ፍሬዎች የተምሳሌትነት ጉዞ የትውልድ ብልፅግና ነው የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።
በተጨማሪም መጋቢት 24 የኢትዮጵያ ለውጥ መነሻና ብልፅግና መሠረት ነው፣ መጋቢት 24 በመስዋዕትነት መጣ በመስዋዕትነት እንጠብቀዋለን የሚሉ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው።