የሀገር ውስጥ ዜና

በምስራቅ ሀረርጌ ዞንና ማያ ከተማ በሀገራዊ ለውጡ ለተገኘው ስኬት እውቅና የሚሰጥ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

By Yonas Getnet

April 02, 2026

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት አስመልክቶ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን እና ማያ ከተማ አስተዳደር በለውጡ ለተገኘው ድልና ስኬት እውቅና የሚሰጥ ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተሳተፉ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በመጋቢት 24 ተምሳሌታዊ ጉዞ እና መሰረታዊ ርምጃ የተመዘገቡ ስኬቶችን አድንቀዋል።

በለውጡ መንግሥት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ተግባራትን በመደገፍ፣ በቀጣይም የተሻለ ስራ እንዲሰራ ከመንግሥት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ የሚያረጋግጡ መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛል።

በዚህም በመጋቢት 24 ፍሬ ወደ ተምሳሌታዊ ጉዞ፣ ጠንካራ መሰረት የተምሳሌትነት ጉዞ ስንቅ፣ መሰረት ባለው ርምጃ ወደ ተምሳሌትነት፣ መጋቢት 24 የተምሳሌታዊነታችን መሰረትና መፍለቂያ ነው፣ የመጋቢት 24 ፍሬዎች የተምሳሌትነት ጉዞ የትውልድ ብልፅግና ነው የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።

በተጨማሪም ለውጡ የጥላቻ ሳይሆን የፍቅር ነው፣ ለሀገር ሰላምና ልማት በጋራ እንቆማለን፣ መጋቢት 24 የኢትዮጵያ ለውጥ መነሻና ብልፅግና መሠረት ነው፣ መጋቢት 24 በመስዋዕትነት መጣ በመስዋዕትነት እንጠብቀዋለን የሚሉ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው።

በተስፋዬ ኃይሉ