የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ታዬ ከቻይና ብሔራዊ ኮንግረስ ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ኃላፊ ጋር ተወያዩ

By abel neway

April 03, 2026

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በቻይና ብሔራዊ ኮንግረስ ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ኃላፊ ዉ ዊሁዓ የተመራው ልዑክ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሁለቱ ወገኖች በሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ግንኙነትን ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

በተለይም በኢትዮ ቻይና የንግድ እና ኢንቨስትመንት ላይ በትኩረት መምከራቸውን የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።