የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ አህመድ ሺዴ ከቻይና አቻቸው ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

April 03, 2026

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ ከቻይና የገንዘብ ሚኒስትር ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ የዕዳ ሽግሽግን በተመለከተ፣ በኢትዮጵያ ያሉ ፕሮጀክቶችን ግንባታ ማፋጠን በሚቻልባቸው እንዲሁም የቻይና መንግስት የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያን ጨምሮ በቁልፍ የፕሮጀክት ኢኒሼቲቮች ላይ ድጋፍ ማድረግ በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስሩ አህመድ ሺዴ ውይይቱ ጠቃሚ እንደነበር ጠቅሰው፤ በውይይቱ ላይ የተደረሰው ስምምነት ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መጠናከር ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል።

ከቻይና መንግሥት ጋር በቅርበት በመስራት የሁለቱን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡

በውይይቱ ሁለቱ ወገኖች የዕዳ አያያዝ ስምምነት ለመፈራረም፣ የፕሮጀክት ትግበራን ለማፋጠን እና ለቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን የፋይናንስ እና ቴክኒካል ድጋፎችን ለማድረግ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡