አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ሕብረተሰቡ ደረጃቸውን ባልጠበቁ፣ ጥራት እና ደህንነታቸው ያልተረጋገጡ ምርቶችን እንዳይጠቀም አሳስቧል።
ባለስልጣኑ ጥራቱና ደህንነቱ የተረጋገጠ የምግብ ምርት ለሕብረተሰቡ እንዲደርስ ለማስቻል በምግብ ምርቶች አመራረት፣ አቀነባበር እና ስርጭት ሂደት እና ህገወጦችን በመቆጣጠር ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለማረም የቁጥጥር ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጿል።
በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች በተደረገ የቁጥጥር ስራ በአጠቃላይ 570 የንግድ ተቋማት ላይ ጥብቅ ፍተሻ መደረጉን ገልጾ÷ ሕገ ወጥ የሆኑና አስገዳጅ የገላጭ ጽሑፍ መስፈርት ያላሟሉ ምርቶች ለገበያ መቅረባቸውን አረጋግጧል።
በዚህም 32 የገበታ ጨው፣ 19 የምግብ ዘይት፣ 6 የለውዝ ቅቤ፣ 6 የማር የምርት አይነቶች እንዲሁም የከረሜላ፣ የዱቄትና የህፃናት ተጨማሪ ምግቦች ደረጃቸውን ያልጠበቁ ሆነው በገበያ ቁጥጥር ወቅት እንደተደረሰበት አመልክቷል።
ሕብረተሰቡ የሚገዛው ምርት በግልጽ የሚታይ የገላጭ ጽሑፍ፣ የአምራች መረጃ፣ የምርት ዝርዝር መረጃ፣ መለያ ቁጥር (Batch Number) እና የጥራት ምልክት የለጠፈ መሆኑን ማጣራት እንዳለበትም አስገንዝቧል።
ባለስልጣኑ ከስር የተዘረዘሩትን የምግብ ምርቶች መስፈርቱን ያላሟሉ፣ ያልተመዘገቡ፣ ጥራትና ደህንነታቸው ያልተረጋገጡ ሕገ ወጥ የምግብ ምርቶች መሆናቸውን በመግለጽ ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ባወጣው መረጃ አሳስቧል።
በዚህም መሰረት፡-
ጨው ዓይነት 👉 ሰይፋ የገበታ ጨው 👉 ቲና የገበታ ጨው 👉 እሙሹ የገበታ ጨው 👉 ቃሊ የገበታ ጨው 👉 አዮዲን የገበታ ጨው 👉 እኑ የገበታ ጨው 👉 አራዳ የገበታ ጨው 👉 ንጉስ የገበታ ጨው 👉 ሀሮት የገበታ ጨው 👉 ኩል የገበታ ጨው 👉 አሜን የገበታ ጨው 👉 ሰቦኑማ የገበታ ጨው 👉 እቱ የገበታ ጨው 👉 መክሊት የገበታ ጨው 👉 ዳግም የገበታ ጨው 👉 መርሰን የገበታ ጨው 👉 ኒሀል የገበታ ጨው 👉 ሊቅ የገበታ ጨው 👉 ስካይ የገበታ ጨው 👉 ናፊ የገበታ ጨው 👉 አቤ የገበታ ጨው 👉 ሳሮማ የገበታ ጨው 👉 ፀሐይ የገበታ ጨው 👉 ማሩ የገበታ ጨው 👉 ንጉስ የገበታ ጨው 👉 እንቁ የገበታ ጨው 👉 ሰኒ የገበታ ጨው 👉 ሚያዋ የገበታ ጨው 👉 ስኬት የገበታ ጨው 👉 ሔራል የገበታ ጨው 👉 ቤዝ የገበታ ጨው 👉 ገዳ የገበታ ጨው
የምግብ ዘይት ዓይነት 👉 ምስራቅ ፀሐይ 👉 ቃል ንፁህ የምግብ ዘይት 👉 አፍራን 👉 ኒያ 👉 ሪሃ ንፁህ የምግ ዘይት 👉 ኤአይ ሻኪር 👉 ኤ1-ኑር 👉 ጥራ ንፁህ የምግብ ዘይት 👉 ረዲ ንፁህ የምግብ ዘይት 👉 አያን 👉 ሳፊያ 👉 እሰይ የተጣራ የምግብ ዘይት 👉 አማን 👉 ላምሮት ኬኬ 👉 እድገት 👉 ራኒያ 👉 ሸገር ዘይት 👉 ሀይላለ 👉 ፍፁም የተጣራ
ከረሜላ ዓይነት 👉 ቡርቃ ሎሊፖፕ 👉 አዩ ፓፕ 👉 አፍሪ 👉 ዴሉክሴ
የለውዝ ቅቤ 👉 ሀራ የተፈጥሮ ለውዝ ቅቤ 👉 ሶራ የተፈጥሮ ለውዝ ቅቤ 👉 ብሉ የለውዝ ቅቤ 👉 ስዊት ክሬም የለውዝ ቅቤ 👉 ሉሲ የለውዝ ቅቤ 👉 ስንቅ የለውዝ ቅቤ
ማር 👉 ቤዛ ማር እና የማር ውጠየቶች 👉 ውብሸት የማር ጠጅ 👉 ጂጂ ማር 👉 አምባሰል ነጭ ማር 👉 የኢሉባቦር ማር